አገልግሎታችንን ይቀላቀሉ

ኪዳን: እሁድ ጠዋት 07 ፡ 00 AM – 08 ፡ 00 AM
ቅዳሴ : እሁድ ጠዋት 08 : 00 AM – 11 : 00 AM

የዚህ ሳምንት የቅዳሴ መርሃግብር

“…ወተወለጠ ራእዩ በቅድሜሆሙ ወአብርሃ ገጹ ከመ ፀሐይ ወአልባሲሁኒ ኮነ ጸዐዳ ከመ በረድ፤ በፊታቸውም ተለወጠ ፊቱም እንደ ፀሐይ አበራ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ኾነ።”
 
እንኳን ለኹለተኛው ሱባዔ ፍልሰታ እንዲሁም ለበዓለ ደብረ ታቦር (ቡሄ) በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!
 
በዚህች ሰንበት የኹለተኛው ሱባዔ አጋማሽና ክብር ይግባውና የጌታችንና የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዐበይት በዓላት መካከል ብርሃነ መለኮቱን ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት የደብረ ታቦርን በዓል በጸሎተ ቅዳሴው በምኅላና በምስጋና እናከብራለን።
 
📆   እሑድ ነሐሴ 11 (Sun, August 17)
⏰   ከጠዋቱ 2 ሰዓት (8 AM) ጀምሮ
⁉️  경기도 광명시 영당로22번길 23