እንኳን ወደ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገጽ በሰላም መጣችሁ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የደቡብ ኮሪያና የሩቅ ምሥራቅ ሀገረ ስብከት

“ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ።”

 መዝ ፩፪፪ : ፩

የደብር አስተዳዳሪው መልእክት

“ክቡራንና ክቡራት እንኳን ወደ ድረ ገጻችን በሰላም መጡ። ድረ ገጻችንን ስለ ጎበኙ ታላቅ ደስታ ይሰማናል። የደቡብ ኮርያ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከ2019 ዓም ጀምሮ ልዩ ልዩ መንፈሳዊ አገልግሎትችን ስታበረክት ቆይታለች። ይህንን አገልግሎቷን ዘመኑን በዋጀ መንገድ ለምእመናኖቿ ለማዳረስ ይህንን ድረ ገጽ ተግባራዊ አድርጋለች። ቤተ ክርስቲያናችን ምዕመናን በመንፈሳዊ ሕይወታቸው እንዲያድጉና በደቡብ ኮሪያ የተወለዱ ህጻናትም ሃይማኖታቸውን ፣ ሀገራቸውንና ባህላቸውን እንዲረዱ ብሎም በመንፈሳዊ ሕይወት ተኮትኩተው እንዲያድጉ ትተጋለች። ቤተ ክርስቲያን በዚህ ድረ ገጽ አማካኝነት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና መሠረት ልዩ ልዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶችን ትሰጣለች። በዚህ የሚሰጠው አገልግሎት የውጭ ዜጎችንም ጭምር ተደራሽ የሚያደርግ መንፈሳዊ አገልግሎት ነው። መንፈሳዊ አገግሎታችን የበለጠ እንዲጎለብትና ተደራሽ እንዲሆን ለሌሎች ማጋራትን ጨምሮ ሐሳብ አስተያየታችሁ እንዳይለየን በቤተ ክርስቲያናችን ስም ለማስታወስ እንወዳለን።”
 

መልአከ ስብሐት ቀሲስ ነጋሢ ግደይ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ ኮሪያ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም አስተዳዳሪ

መርሐ ግብሮች

መጪ ልዩ ክንውኖች

Days
:
Hours
:
Minutes
:
Seconds

ያለፉ ክንውኖች

ወደ ማኅበራችን ይቀላቀሉ

ቤተ ክርስቲያናችን የምትሰጣቸው አገልግሎቶችን ለማግኘት ምእመናን በዚህ ድረ ገጽ አማካኝነት የአባልነት መሙያ ቅጽ ሞልተው መላክ ይጠበቅባቸዋል።

ኆኀተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያንን ለማግኘት

ይጎብኙን

ቤተክርስቲያናችን የሚገኝበት አድራሻ፦ 23, Yeongdang-ro 22beon-gil, Gwangmyeong-si, Gyeonggi-do.

በኢሜይል ያግኙን

በዚህ የኢሜይል አድራሻ ይጻፉልን፦ info@lightofsaintmary.kr

ይደውሉልን

በዚህ ቁጥር ይደውሉልን፦ +82 2-1234-5678