ስለ ቤተ ክርስቲያኒቱ

የደቡብ ኮሪያ የኆኀተ ብርሃን ቅድስት ማርያም እ.ኤ.አ. በ2019 በበጹዕ አቡነ ድሜጥሮስ የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቡራኬ የተመሰረተች ደብር ናት። ቤተ ክርስቲያኒቱ ከተመሠረተችበት ጊዜ አንሥቶ ከምሥጢራት በተጨማሪ ልዩ ልዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶችን ለህዝበ ክርስቲያኑ እየሰጠች ትገኛለች። ቤተ ክርስቲያኒቱ ከተመሠረተች ጀምሮ በደቡብ ኮሪያ ብቻ ሳይሆን በልዩ ልዩ በሩቅ ምሥራቅ ሀገራት የሚገኙ ህዝበ ክርስቲያኖች የበይነ መረብ መንፈሳዊ አገልግሎቶችና ትምህርቶች ስትሰጥ ቆይታለች ፤ አሁንም እየሰጠች ትገኛለች።

የእምነት አቋም

“ሁሉን በያዘ ሰማይንና ምድርን የሚታይና የማይታየውን በፈጠረ በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር እናምናለን። ዓለም ሳይፈጠር ከርሱ ጋር በነበረ የአብ አንድ ልጁ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስም እናምናለን። ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፣ ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ፤ የተፈጠረ ያይደል የተወለደ፤ በመለኮቱ ከአብ ጋር የሚተካከል። ሁሉ በርሱ የሆነ ያለ እርሱ ግን ምንም የሆነ የለም። በሰማይም ያለ በምድርም ያለ። ስለእኛ ስለሰው ስለ መዳኛችን ከሰማይ ወረደ። ከመንፈስ ቅዱስ የተነሣ ከቅድስት ማርያም ፈጽሞ ሰው ሆነ። ሰው ሆኖ በጰንጤናዊበጲላጦስ ዘመን ስለእኛ ተሰቀለ። ታመመ፤ ሞተ፤ ተቀበረም፤ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፤ በቅዱሳትመጽሐፍት እንደ ተጻፈ። በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ። ዳግመኛ ሕያዋንን ሙታንንም ይገዛ ዘንድበጌትነት ይመጣል። ለመንግሥስቱም ፍጻሜ የለውም። ጌታ ማሕየዊ በሚሆን ከአብ በሠረፀ በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን። እንሰግድለት እናመሰግነውም ዘንድ፤ ከአብና ከወልድ ጋር በነብያት የተነገረ።ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰብዋት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንምእናምናለን።ኃጥያትን ለማስተሥረይ በአንዲት ጥምቀት አናምናለን።የሙታንንም መነሣት ተስፋ እናደርጋለን የሚመጣውንም ሕይወት ለዘላለሙ አሜን።”

ብጹዕ አቡነ ያዕቆብ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የደቡብ ኮሪያና የሩቅ ምስራቅ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ቀሲስ መምህር ስብሐት ነጋሲ

የኆኀተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ

ቀሳውስት እና ዲያቆናት